ግባችን ወንጌልን መስበክ ነው፡ ማለትም፡ የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ የማዳን መስዋዕት በማመን የሰው ከእግዚአብሔር ጋር የመታረቁን የምስራች ወንጌልን መስበክ ነው። ይህ እምነት ዳግም መወለድን፣ መቀደስን፣ በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና የዘላለም ሕይወት ተስፋ መኖርን ያስከትላል። የወንጌል ድምጽ ሬድዮ ዓላማው የእግዚአብሔር ቃል የሆነውን የመጽሐፍ ቅዱስን ዘላለማዊ እሴቶች በማስተዋወቅ ለህብረተሰቡ መንፈሳዊ፣ ሞራላዊ እና ባህላዊ ለውጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ ነበር።
አስተያየቶች (0)